ህመምን በአፋጣኝ ከማስታገስ የሚገርም ፈገግታን እሰከማላበስ
የላቀ የጥርስ ህክምና ደረጃ በኢትዮጵያ
በአዲስ አበባና በሌሎቸም የኢትዮጵያ ክፍሎች ያስተዋሏቸውን ተመጣጣኝ፣ የተሟላና ጥራቱን የጠበቀ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ክፍተቶችን ለመሙላት በማሰብ ያኔት የጥርስ ህክምና ክሊኒክ በ2008 ዓ.ም በዶ/ር አመልማል መንግስቱ በአዲስ አበባ ተመሠረተ። ክሊኒኩም በተመሰረተ በአጭር ዓመታት ውስጥ በጥርስ ህከምና አገልገሎቶቹ ተቀባይነት እያገኘ መምጣት በመቻሉ የተነሳ እንዲሁም በአገልግሎቱ ብቃቱ፣ በፈጠረው የተቀናጀ የህክምና ቡድኑ ትጋት፣ በምቹና ሳቢ የህክምና መስጫ ቦታዎቹ፤ ባስገባቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተቆጣጣሪ ባለሥልጣን መስፈርቶች በማሟላት ደረጃውን በማሻሻል ልዩ የጥርስ ህክምና ከሊነሊክ ለመሆን በቅቷል።
በአሁኑ ወቅት ሁለተኛና ሶስተኛ ቅርንጫፎቹን በአዲስ አበባ ከተማ ያቋቋመ ሲሆን የአገልግሎቶቹን ዓይነቶች ይበልጥ ለማስፋት ዘመኑ ያፈራቸውን ዲጂታል የጥርሰ ኤክስሬይ፣ የአፍ ውስጥ ስካነር፣ የተቀናጁ የጥርስ ህከምና መሰጫ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች ሥራ ላይ አውሏል። በተጨማሪም እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ በኮምፒዩተር ዲዛይን የታገዘ ቋሚ ወይም ገቢና ወጪ አርቴፊሻል ጥርሶችን ዚረኮኒያን ጨምሮ በተለያዩ ማቴሪያሎች መስራት የሚችል ላቦራቶሪ አቋቁሟል።
ያኔት ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ በአገር አቀፍ ደረጃ ለጤና ተቋማት በወጣውን የአፈፃፀም ደረጃ ምዘና አንደኛ መሆን በመቻሉ ከአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የ2017 ዓ.ምን የአንደኛ ደረጃ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ለማግኘት የቻለ ሥመጥር የጥርስ ህክምና ማዕከል ነው።
ዶ/ር አመልማል መንግስቱን ያግኙ (የጥርስ ቀድዶ ህክምና ሐኪም)
የያኔት ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ከ10 ዓመታት በላይ የካበተ የጥርስ ህክምና ልምድ ያላቸው ዶ/ር አመልማል መንግስቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የጥርስ ህክምናን
ከሚያራምዱ የመጀመሪያ ረድፍ መሪዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። ዶ/ር አመልማል የያኔት ልዩ የጥርስ ህክምና መስራችና ባለራዕይ መሪ ከመሆናቸውም ባሻገር የታከሚዎቼ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉና
ታመኘነትን የተላበሱ፣ ለሙያው የተሰጡ እና ለጥርስ ህክምና ዘመናዊነትና ዕድገት ቆርጠው የተነሱ በመሆናቸውም ይታወቃሉ።
ዶ/ር አመልማል
መንግስቱ ዘመናዊ የጥርስ ህክምና
ዕውቀቶችና ክህሎቶችን
ከታማኝ የታካሚ እንክብካቤ ጋር በማዋሃድ ግለሰቦችንና ቤተሰቦችን ሁልጊዜም ጤናማ
ጥርሶችና የአፍ ውስጥ
ጤንነት እንዲሁም የራስ
መተማመንን የበለጠ የሚያጎለብት ፈገግታ እንዲኖራቸው ያበረታታሉ፤
ይተጋሉ።
ዶ/ር አመልማል መንግስቱን ያግኙ (የጥርስ ቀድዶ ህክምና ሐኪም)
ያኔት ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ መስራች እና ዋና
ከ10 ዓመታት በላይ የካበተ የጥርስ ህክምና ልምድ ያላቸው ዶ/ር አመልማል መንግስቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የጥርስ ህክምናን ከሚያራምዱ የመጀመሪያ ረድፍ መሪዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። ዶ/ር አመልማል የያኔት ልዩ የጥርስ ህክምና መስራችና ባለራዕይ መሪ ከመሆናቸውም ባሻገር የታከሚዎቼ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉና ታመኘነትን የተላበሱ፣ ለሙያው የተሰጡ እና ለጥርስ ህክምና ዘመናዊነትና ዕድገት ቆርጠው የተነሱ በመሆናቸውም ይታወቃሉ። ዶ/ር አመልማል መንግስቱ ዘመናዊ የጥርስ ህክምና ዕውቀቶችና ክህሎቶችን ከታማኝ የታካሚ እንክብካቤ ጋር በማዋሃድ ግለሰቦችንና ቤተሰቦችን ሁልጊዜም ጤናማ ጥርሶችና የአፍ ውስጥ ጤንነት እንዲሁም የራስ መተማመንን የበለጠ የሚያጎለብት ፈገግታ እንዲኖራቸው ያበረታታሉ፤ ይተጋሉ።
የጥርስ ህክምና አገልግሎቶቻችንን ይወቁ
ተልኳችን ጥራቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ እና ታካሚን ማዕከል ያደረገ የጥርስ ህክምና አገልገሎት መስጠት ነው። እኛ ማንኛውም ሰው ጤናማና የሚያምር ፈገግታ ይገባዋል የሚል እምነት አለን። በዚህ ረገድ የኛ ኃላፊነት ይህንን ዕውን ለማድረግ መትጋት ነው። ትኩረታችን ማንኛውም ታካሚ የሚሻውን ፈገግታ እንዲላበስ ሙያዊና ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ ማማከርና ማከም ነው።
ቀጠሮ ያሲዙ
የመከላከያ (Preventive) የጥርስ ህከምና
እኛ በሽታ እንዳያጋጥም አስቀድሞ መጠንቀቅ ወይም መከላከል ብዙ ዋጋ የማያስከፍል ፍቱን መድኃኒት ነው ብለን እናምናለን። በዚህም መርህ መሰረት ጥርስ፣ ድድ እና በአጠቃላይ የአፍ ውስጥ አካላት ለተለያዩ እንደ መቦረቦር፣ መበስበስ/መፈረካከስ፣ የአፍውስጥ ካንሰር፣ የድድ መድማት/መቆጣት ወይም ለመሳሰሉ ችግሮች እንዳይጋለጡ የሚያደርጉ የመከላከያ ህክምናዎችን አዘጋጅተን እንጠብቅዎታለን።
ጥርስን የማደስ (Restorative) ህከምና
ይህ ጥርስን የማደስ የህክምና አገልገሎት በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዱ፣ አቅማቸውን አጥተው በመፈረካከስ ላይ ያሉ ወይም ከቦታቸው ተነቅለው የጠፉ ጥርሶችን ቀድሞ በነበሩበት ሁኔታ በመመለስ በቀላሉ ለማኘክ፣ ፈገግታን በኩራት ለማካፈል እና ወደፊት ሊከሰቱ የሚቸሉ ተመሳሳይ ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችሉ የተቦረቦሩ ጥርሶቸን ከመሙላት ሰው ሰራሽ የጥርስ አክሊሎች መጠናቸው ለቀነሰ እንዲሁም ከደህና ጥርሶች መካከል ለጠፉ ደግሞ ድልድዮችን አዘጋጅቶ በማኖር የሚካሄዱ የህክምና አይነቶችን ያካተተ ነው። .
ውበት-ተኮር ጥርስ ህክምና
ሰዎች ብዙውን ጊዜ አተኩረው የሚመለከቱት
በጥርስዎ ውበት የተሞላውን ፈገግታዎን ነው። የውበት-ተኮር ጥርስ ህክምና ዋና ዓላማውም ውበትን ማላበሰስ ሲሆን ለዕይታ የሚማርክ
የጥርስ አቀማመጥን፣ የድድና የአነካከስ መስተካልን እንዲሁም የጥርስን ንጣት፣ መጠንና አደራደርን ማሻሻል ነው ።
ጥርሰዎን ሃጫ በረዶ ለማስመሰል፣ ቀጥ ቀጥ ለማድረግ መጠናቸውንና አደራደራቸውን
ለማሳመር ሲፈልጉ ያኔት የጥርስ ህክምና ክሊኒክን ይጎበኙ! ፍላጎትዎን ያሳኩና እንደልብዎ ይሳቁ!
የጥርስ ንቅለ-ተካላ ህክምና
የጥርስ ንቅለ-ተካላ ከጥርስ፣ ድድና መነጋጭላ ጋር የያያዙ ከበድ ያሉ ችግሮችን ለማከም የሚያስችሉ ፐሮሲጀሮችን የያዘ ሲሆን ጥርስ መንቀል፣ ሰው ሰራሽ የጥርስ መያዣ ቋሚ ተተካዮችን ማኖር፣ የተዛባ መንጋጭላን ማቃናትና የመሳሰሉ ተጠቃሽ ፕሮሲጀሮች ናቸው። ይህ ህክምና ተጨማሪ ሥልጠናና ልምድ ባላቸው የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች የሚከናወንና በአደጋም ይሁን በሌሎች ህመሞች ምከንያት የሚከሰቱ የጥርስ በቦታው አለመገኘትን ለመተካትና ለመጠበቅ አንዲሁም የጥርስን ተፈጥሯዊ አገልግሎትና ገፅታን ለመመለስ ያስችላል።
Unveil Our Exclusive Dental Treatments
Our mission is to provide high-quality dental care in a comfortable and welcoming environment. We believe that everyone deserves a healthy, beautiful smile, and we are committed to helping our patients achieve that goal.
Unveil Our Exclusive Dental Treatments
Our mission is to provide high-quality dental care in a comfortable and welcoming environment. We believe that everyone deserves a healthy, beautiful smile, and we are committed to helping our patients achieve that goal.
በያኔት ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ለምን ይመርጣሉ?
በያኔት ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ የጥርስዎን ጤንነትና ፈገግታዎን መጠበቅ ሥራችን ብቻ ሳይሆን የሙያ ትጋት ምልክታቸንም ነው። አድቫነስድ ቴክኖሎጂን፣ ግለሰባዊ እንክበካቤንና የእንኳን ደህና መጡ ስሜትን የሚያላብሱ ክሊኒካዊ ሁኔታዎቸን በማጣመር ከመሰረታዊ የአፍ ውስጥ ጤንነት ህክምና እጅግ የላቁ ዘመናዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎቶችን እንሰጣለን። የሚከተሉት ነጥቦች እኛን ልዩ ያደርጉናል:
የሚተማመኑበት በክህሎት የሚከናወን አገልግሎት
የጥርስ ህክምና ቡድናችን አባላት (ኤከስፐርት
የጥርስ ሃኪሞች) በቀደሞ መከላከል፣ ወደነበረበት በመመለስ እና በውበት-ተኮር የጥርስ ህክምናዎች ላይ ስፔሻላይዝድ ያደረጉ
ናቸው። ባላቸውም አድቫንስድ ሥልጠናዎችና የካበተ ልምድ ምክንያት በታከሚው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ከፍተኛ ጥራት ያለው
አገልግሎትን ለማበርከት የተሰጡ ናቸው። ይህንንም ለማሳካት እንችል ዘንድ ጊዜያቸንን ሳንቆጥብ የእያንዳንዱ ታካሚያችንን
ፍላጎትና ግብ በመረዳት የህክምና እቅድ እናዘጋጃለን፤ በመሆኑም ህክምናዎን እስኪጨርሱ ባሉት በእያንዳንዱ ሂደት የመተማመን
ሰሜት ይኖሮታል።
በቀጠሮዎ መሠረት ቀልጣፋ አገልግሎት
የተሳለጠ የሥራ ፍሰትን ከዘመናዊ ቴክኖጂዎቻችን ጋር በማቀናጀታችን ንቅለ-ተከላንና ወደነበረበት የመመለስ ህክምናዎችን ጨምሮ በተባለው የቀጠሮ ሰዓት ህክምናን መስጠት አስችሎናል። ያለምንም ጥበቃና መዘግየት የጥራት ደረጃው በተጠበቀ ህክምና የራስ መተማመንዎን በፈገግታዎ ይመልሱ።
ለእያንዳንዱ ተደራሽ የሆነ የጥርስ ህክምና አገልግሎት
የአፍ ውስጥ ጤንነትና ፈገግታ እንዲሁም የአእምሮ ሰላም ያሳስባል። እኛ የእርሶዎ ትኩረት ጤንነትዎ ላይ እንጂ ክፍያ ላይ እንዳይሆን የተለያዩ የአከፋፈል አማራጮችን በማቅረብ ተመጣጣኝ የአገልግሎት ከፍያ ያለው ህከምና እንዲያገኙ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን።
በያኔት ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ለምን ይመርጣሉ?
At Yanet Specialty Dental Clinic, we go beyond basic dentistry — delivering care that’s advanced, accessible, and deeply personal. Here’s what sets us apart:
Expertise You Can Trust
Our team includes highly trained specialists in restorative, implant, and cosmetic dentistry. With years of experience and a commitment to excellence, we tailor every treatment to meet your unique needs.
Same-Day Solutions
We use advanced technology and efficient workflows to offer same-day treatments, including implants and restorations. You don’t have to wait weeks for results — we help you smile confidently, faster.
Affordable, Flexible Care for All
We believe dental care should never be out of reach. That’s why we offer flexible payment plans, transparent pricing, and in-house financing — so you can prioritize your health without financial stress.
ሥራዎቻችን ይመልከቱ፣ የሥራ ቡድናቸንን ያግኙ እንዲሁም እያደገ የመጣውን የማህበራዊ ሜዲያ ታዳሚዎቻችንን ይቀላቀሉ
From Urgent Relief to Stunning Smiles!
Innovation
How smiles come to life
Focus
Building smiles
22%
Reaching new heights in dental care
+12
Transform Your Smile
Innovation
How smiles come to life
Focus
Building smiles
22%
Reaching new heights in dental care
+12
Transform Your Smile
እንዴት የሰዎችን ፈገግታ እየለወጥን እንደሆነ ይመልከቱ!
ፈገግታችንን በመመለስ
የደስታችን ባለቤት እንሁን
የአፍ ውስጥ ጤንነታችንን
በመጠበቅ በሽታን እንከላከል
ማህበራዊ ኃላፊነትን
መወጣት በተግባር
Smiles That Speak for Themselves
- “ሳቅ የደስታ ምንጭ ነው ሳቄን ለማሳማር ያኔትን ምርጫዬ አድርጌአለሁ። እንደእኔ ጥርሳችሁን ለማሳማር ያኔት የጥርስ ህክምናን ምርጫችሁ አድርጉ”
- — ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል
- “እጅግ በጣም ነው የወደድኩት። እንደእኔ ያማረ ጥርስ መሰራት ከፈለጋችሁ ምርጫችሁን ያኔት እንድታደርጉ እጠቁማችኋለሁ”
- — አቀናባሪ ስማገኘሁ ሳሙኤል
- ል
- — አርቲስት በዕውቀቱ ሰውመሆን (ጉስም)
- “ሳቄን ደስታዬን ነው የመለሺልኝ። በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ያክብርልኝ እጅሽ ይባረክልሽ።”
- — አርቲስት ኃይማኖት ግርማ
የእርስዎ ፈገግታ - የኛ ትኩረት ነው
እኛ እዚህ ያለነው በማንኛውም የህክምናዎ ሂደት ልደግፍዎ፤ የተሻለ የአፍ ውስጥ ጤንነተዎ እንዲጠበቅ፣ በራስ መተማመንዎ እንዲመለስልዎት እና የሚወዱትን ፈገግታዎን እንዲያገኙ ለመረዳት ነው።
ልዩ እንክብካቤ
የተረጋጋ፣ ታካሚን ማዕከል ያደረገና መቾትዎን ያስቀደመ ከፍተኛ ጥራት ያለው የጥርስ ህክምና ለመስጠት እንተጋለን።
ታካሚ-ተኮር አገልግሎት
እያንዳንዱ ፈገግታ የተለየ እንደመሆኑ መጠን የኛም ህክምና እንደዛው የተለየ ነው። ጊዜ ወስደን ፍላጎትዎን በመረዳት የህክምናዎን ዕቅድ እናዘጋጅልዎታለን።
ዘመናዊ መፍትሄዎች
ዘመናዊ የጥርስ ህክምና ቴክኖሎጂን ከላቀ ክህሎት ጋር በማቀናጀት አስተማማኝ፣ ተፈጥሯዊ ዕይታ የተላበሰና የረጅም ጊዜ ጠቀሜታ ያለው መፍትሄ እንሰጥዎታለን።
ጤናማ ፈገግታ የደሰታና የተሟላ ጤንነት ነፀብራቅ ነው!
Join us and enjoy the benefits of a healthy smile.
